ለ አእምሮ - መጽሔት © ስለ ፖለቲካና ኢኮኖሚ፣ ባሕልና ታሪክ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ለመዝናናት – ሙዚቃ ሲንቆረቆር….

In ኪነ፥ጥበብ on September 27, 2013 at 1:00 am

ለመዝናናት –

ሙዚቃ ሲንቆረቆር….

music-notes

ከፖለቲካ ውጭ (ይህ ነው የሰው ልጆች ሌላው ችሎታ) ከእሱም ከፖለቲካው የበለጠ የአንድ አገርን ሕዝብ ውስጣዊ ሰሜት ቀሰቅሰው የሚያስተሳስሩአቸው ብዙ ነገሮች አሉ። አንደኛው አለጥርጥር ልብን የሚነካው ሙዚቃ ነው። ሙዚቃ ደግሞ በስፋትና በጥልቀቱ ድንበርም አልፎ ሄዶ ( አብዮታዊ መዝሙር እኮ እዚህ ግባ የማትባል ውስን ነገር ናት እሱዋን እንርሳ!) የሰው ልጆችን የበለጠ ያቀራርባል።ያስተሳስራል። ሌላው ሁለተኛው ግሩም ልብ- ወለድ የፍቅር ድርሰትና ድራማ ነው። እነሱ እንዲያውም „ዩኒቨርሳል“ ናቸው። ፊልም አለ። ግጥም። እስክስታና ጭፈራ…

ቀደም ሲል በአለፈው ዓመት ደስ የሚለውን „አቤት አቤት…“ የሚለውን የወጣቶች ጨዋታ ሰምተናል። አሁን ደግሞ እነሱን የመሰሉትን አዲሱን „የጃኖ ባነድ“ ሙዚቃ በዚህ በመስከረም ወር አዳምጠን እጅግ ደስ ብሎናል። ዱሮውንም -ይህ ባህል በዚያ በደርጎች አብዮታዊ መዝሙር ተቀየረ እንጂ- ዱሮውንም በመስከረም፣ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በምሽቱ ላይ ስንት አዳዲስ ሙዚቃዎችን የምንሰማበት ቀን ነበር። አሁን በአዲሱና በወጣቱ ትውልድ ይህ ነገር እንደገና መጀመሩ ደስ የሚያሰኝ ነው። ምን ይላሉ እነዚህ ወጣቶች?

አይራቅ የምትመጪበት ቀን
አይራቅ የምትመጪበት ቀን
አይራቅ የመገናኛው ቀን
አይራቅ የምትመጪበትቀን
ፀሃይ ካይኖቼ ስትጠፋ
ነገን ስጠብቅ ሁሌ በተስፋ
ነገም ነግቶ ይመሻል
ሁሉ መጥቶ አንቺ ብቻ ቀርተሻል
አይራቅ….(Chorus)”

http://janoband.com/fr_home.cfm

መልካም መዝናናት….

ጃኖመጣ

(ለማዳመጥና ለውዳሴ ጃኖ፣ እዚህ ይጫኑ !)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s